“ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም”
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ መዝ( ፸፯÷፷፭)
በቀሲስ አድማሴ መኮንን
በትራክት መልክ የተዘጋጀውን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ።
ታላቁ አባት ቅዱስ ኤፍሬም ሃይማኖተ አበው በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ ፵፯ ክፍል ፩ ቁጥር ፮ ላይ ልዩ በሚሆን ድንቅ በሚያሰኝ መለወጥ ይስማማው በነበረ ሥጋ በተወለደው ልደት ወደ አልተለመደው ነገር /ወደ ሞት/ ወደ መስቀል ደረሰ ( ኢሣ ፱÷፮ _ ፯):: እኛን የሚመስል ሥጋን ገንዘብ አደረገ ይኸውም ከሁሉ ጋራ አንድ ነው ከባህርያችን የተገኘው አንድ አካል አንድ ባህርይ የሆነ እርሱ ሕማም ሞት የሌለበት ሲሆን በሥጋ ባህርይ ኃጥያት ሳይኖርበት ታመመ ሞተ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጥያት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጥአት አደረግነው(፪ኛቆሮ ፭÷፳፩)“ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ ኃሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሣለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማትን እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም ነገር ግን የባርያውን መለክ ይዞ በሰው ምሣሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ “(ፊልጵ፪÷፭ _ ፱)“