View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: ነገረ ቅዱሳን ::.. Register  Login
ነገረ ቅዱሳን

በዚችም ቀን (ሕዳር ፳፮) የተመሰገነና የከበረ ንጹሕም የሆነ የኢትዮጵያዊ አባታችን የሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ ቅዱስ አባት የትውልድ አገሩ የራውዕይ በምትባል በስተምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ነው፤ በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ይህም ክቡራንና ታላላቅ ከሚባሉት ከዚች አገር ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው። እጅግም ሀብታም ነበር፤ ብዙ ንብረትም አለው በሕጋዊ ጋብቻም ስሟ ዮስቴና የምትባል ብላቴና ድንግልን አገባ። ይቺም የተመረጠች በበጎ ሥራ የተሸለመችና ያጌጠች ናት። ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕግ ባሏ ጋር በንጹሕ ጋብቻ እግዚአብሔርን በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የዋህነትን ትሕትናን ፍቅርን ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ በጾም በጸሎት ተወስና እንደኖረች እንነግራችኋለን።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

ቅዱሳን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከቤቱ ጀምሮ በጽላቱ በጠበሉ ይታሰባሉ። ቤቱ፥ ጽላቱ፥ ጠበሉ የእግዚአብሔር ሲሆን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፥የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጽላት፥ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጠበል ይባላል። በዚህ ሁሉ ስማቸው እየተጠራ እንዲታሰቡ ያደረገ እግዚአብሔር ነው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
  


ነገረ ቅዱሳን

ጥቅምት ፲፬ ቀን የቁስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቴዎዶስዮስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር:: ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም አብደልመሲህ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም ገብረክርስቶስ ማለት ነው። የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ በስተቀኝ ያለውን ምልክት ይጫኑ 

Click the icon to the right to read about Saint Gabra Krestos
 
  


ነገረ ቅዱሳን

የቅድስት አርሴማ ወላጆች አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትናትያስ ይባላሉ:: በፈሪሃ እግዚአብሔር  በአምልኮ ጸንተው በሕጉ ተመርተው የኖሩ ደጋግ ሰዎች ናቸው:: ልጅ አጥተው መካን ሆነው ሲኖሩ ዘር እንዲሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር:: እግዚአብሔርም  ጸሎታቸውን ሰምቶ ደም ግባቷ ያማረ መልከ መልካም የሆነች እንደ ጸሐይ የምታበራ ልጅ ሰጣቸው:: ቅድስት አርሴማ የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ይባላል:: ዲዮቅልጥያኖስ የሮም ቄሳር ሆኖ የነገሰበት (እኤአ ከ284ዓ/ም - 305 ዓ/ም) : አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉበትና አብያተ ጣኦታት ተከፍተው ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ልዩ ልዩ መከራና ሰማዕትነት የሚቀበሉበት ዘመን ነበር::  ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤  ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤  በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ” እንዳለ  ዕብ  11:35-37
  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን



Page 1 of 5First   Previous   [1]  2  3  4  5  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement