View in English alphabet 
 | Wednesday, May 1, 2024 ..:: ነገረ ቅዱሳን ::.. Register  Login
  

ቅዱሳን መላእክት

ከብርሃኑ ጎበና

ቅዱስ ማለት የተለየ፣ የተከበረ፣ የተመሰገነ፣ የተመረጠ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ስንልም የተመሰገኑ፣ ከርኵሳን መላእክት የተለዩ፣ ክቡራን መላእክት ማለታችን ነው፡፡ መላእክት ሁለት ወገን ናቸው፡፡ ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የሆነው የዲያብሎስ ሠራዊት የሆኑት እኩያን መላእክት፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡

መላእክት መቼ ቀን ተፈጠሩ?

መላእክት የተፈጠሩት በመጀመሪያው ቀን በዕለተ እሑድ ነው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አክሲማሮስ /ሃክላኢሜሮን/ ተብሎ በሚጠራው መጽሐፍ እግዚአብሔር መላእክትን በዕለተ እሑድ ፈጥሮ በሦስቱ ሰማያት በኢዮር፣ በራማና በኤረር፤ በከተማ አሥር፣ በነገድ መቶ አድርጎ አሰፈራቸው ብሏል፡፡



አሰፋፈራቸው፡-

ኢዮር፡-
በኢዮር ያሉትን መላእክት በ4 አለቃ አርባ ነገድ ከፈላቸው፡፡ ኢዮርን እንደ ፎቅ ቤት አድርጎ በአራት ከተማ ከፈላት፡፡ በኢዮር በላይኛው ከተማም አሥሩን ነገድ ስማቸውን አጋእዝት ብሎ በመሰየም አለቃቸው ይሆን ዘንድ ሳጥናኤልን ሾመው (10፥1)፡፡ በኢዮር በሁለተኛው ከተማ አሥሩን ነገድ ስማቸውን ሱራፌል ብሎ በመሰየም ሱራፌል የተባለውንም መልአክ አለቃቸው አደረገው (ኢሳ. 6፥2)፡፡ በኢዮር በአራተኛው ከተማ አሥሩን ነገድ ስማቸውን ኃይላት (ጴጥ. 3፥22) በማለት ቅዱስ ሚካኤልን በአለቅነት ሾመላቸው፡፡

ራማ፡-
ራማ በተባለው የብርሃን ሰማይ ላይ ያሉትን መላእክት ሦስት ከተማ አድርጎ ከፍሏታል፡፡ በመጀመሪያ በራማ የሠፈሩት አሥሩ ነገድ ስማቸው አርባብ ይባላል፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በሁለተኛው ከተማ ያሠፈራቸው አሥሩ ነገድ መናብርት ሲባሉ አለቃቸውም ሩፋኤል ነው:: በሦስተኛው ከተማ ያሠፈራቸው አሥሩን ነገድ ስማቸውን ሥልጣናት (1ጴጥ. 3፥22) በማለት አለቃቸው ይሆን ዘንድ ሱርኤል የተባለውን መልአክ ሾሞታል፡፡

ኤረር፡-
ኤረር የተባለውን ሰማይ እንደ ራማ በሦስት ከተማ የከፈለው ሲሆን የቀሩትን ሰላሣ ነገድ በእነዚህ ከተማዎች አሥፍሯቸዋል፡፡ መጀመሪያው ከተማ አሥሩን ነገድ መኳንንት (መዝ. 3/2፥47-10) በማለት ሰደክያል የተባለውን መልአክ አለቃ አድርጎላቸው አሥፍሯቸዋል፡፡ በሁለተኛው ከተማ አሥሩን ነገድ ሊቃናት በማለት አለቃቸው ይሆን ዘንድ ሰላታኤል የተባለውን መልአክ ሾሞታል፡፡ በሦስተኛ ከተማ አሥሩን ነገድ መላእክት (1ጴጥ. 3፥12) ብሎ ሰይሟቸዋል፡፡ አናንያል የተባለውን መልአክም አለቃቸው አድርጎታል፡፡

በእነዚህ በሦስቱ የመላእክት ሰማያት ላይ የሠፈሩት መላእክት በነገድ መቶ ሲሆን በከተማ ደግሞ አሥር ነበሩ፡፡ ከእነርሱም ሰማልያል /ሳጥናኤል/ አንዱን ነገር ይዞ ከክብሩ ወርዷል (ኢሳ. 14፥12)፡፡


Written By: admin
Date Posted: 12/19/2007
Number of Views: 16247

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement