View in English alphabet 
 | Friday, May 3, 2024 ..:: ኅብረ ነገር ::.. Register  Login
  

የውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ


“እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።” ሉቃ 1፥48-49

 

ለተወደዳችሁ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ፤
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!

 

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ ነሐሴ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ጾም በሊቃውንተ ቤ/ክን አባቶች አማካኝነት የእመቤታችንን ውዳሴና ቅዳሴ ትርጓሜ ሲያቀርብ ቆይቷል። ዘንድሮም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዋዜማው ሰኞ ሐምሌ 30 2004 ዓ.ም. አንስቶ ይጀምራል።

ስለዚህ እርስዎም በሰዓቱ በስልክ ጉባኤው ላይ በመሳተፍ ነፍስዎን ቃለ እግዚአብሔር ይመግቡዋት፣ ከወላዲተ አምላክ ውዳሴና ቅዳሴ ይሳተፉ፤ ስለሀገር፣ ወገንና ስለቅድስት ቤ/ክንዎ በጋራ ይጸልዩ። ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም እንዲገኙ ይጋብዙ።

ቀናት፦ ከሰኞ ሐምሌ 30 - ማክሰኞ ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. / August 6-21, 2012
ሰዓት፦ ከምሽቱ 9:00 PM - 10:00 PM PST (ሲያትል ሰዓት)
12፡00 AM - 1:00 AM EST (ዲሲ ሰዓት)

የኮንፈረንስ ቁጥር፦ (712) 432-1001 
Access Code: 428585128# (ለማዳመጥ ብቻ)

 

ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


Written By: admin
Date Posted: 8/4/2011
Number of Views: 7904

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement