View in English alphabet 
 | Friday, April 26, 2024 ..:: ኪነ ጥበብ ::.. Register  Login
  

አማልጅኝ ድንግል ሆይ

በዲ/ን አብነት አረጋ


በገሊላ ቃና በዶኪማስ ቤት
ድንግል አዛኚቱ የአምላክ እናት
እድምተኛው በዝቶ ወይኑ ቢያልቅባቸው
ጥብብ ጭንቅ ሲሉ ማጣፊያው አጥሯቸው
ወይ ጓዳ ሳትገባ ሳትጠይቃቸው

ለምን እንደመጣ ቀድማ በማወቋ
ልቡን በሚያራራ የእናትነት ቋንቋ
ልጄ ሆይ ተመልከት ስማኝ የኔ ጌታ
ዶኪማስ አፈረ ድግሱ ተፈታ
የወይኑ ጋን ደርቆ የለውም ጠብታ
የታደመው ጠጥቶ ሳያገኝ እርካታ
ይገባል ታዳሚ ሊካፈል ደስታ
በኖረበት ሀገር ታፍሮና ተከብሮ
ደግሶ የጠራውን ትናንት ልጁን ድሮ
ውለታ ሊመልስ እሱም ወገን ጠርቶ
ደስታ ተጀምሮ ጨዋታውም ደርቶ
ልክ እንደጅምሩ በስኬት ተቋጭቶ
ተመስገን ሳይሉ ሠርጋቸው ተሳክቶ
ወይኑ በማለቁ ዳር ያደርሳል ያለው
ተክዟል ዶኪማስ አለሁልህ በለው
ብለሽ እንዳማለድሽ ከእፍረት እንዳዳንሽው
ስለእኔም ባዶነት የእኔ ጌታ በይው።
እንደ ድንጋይ ጋኖች እንደ ባዶ እንስራ
እምነት ብቻ ሆኜ የተለየሁ ሥራ
ከእንቅብ በታች ሆኖ ደምቆ እንደሚያበራ
ለማንም ላይጠቅም የብርሃኑ ጮራ
በከንቱ እንደሚነድ እንደ ከንቱ መብራት
እንደ በለሲቱ ፍሬ እንደታጣባት
ለሕይወት ታጭቼ እንዳልሰጥ ለሞት
ዛሬም ተመልከቺ ድንግል የእኔን ጉድለት።
ተመልከቺኝ ድንግል የወይን ጠጄ አልቋል
ልጄ ሆይ በይልኝ ምልጃሽን ይሰማል።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Written By: admin
Date Posted: 11/8/2011
Number of Views: 12689

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement