View in English alphabet 
 | Friday, June 14, 2024 ..:: ስብከተ ወንጌል ::.. Register  Login
ስብከተ ወንጌል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“አላ ሰብእ አልብየ” ሰው የለኝም (ዮሐ 5፥7)


በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ከፈለኝ ወልደጊዮርጊስ


ቤተ ሳይዳ ወይም ቤተሰዳ ማለት የምህረት ቤት ማለት ነው አምስትም መመላለሻ ያላት ማለትም አምስቱ አዕማደ ምሥጢር የሚገኝባት በነዚህ ሁሉ ድህነትን የምትሰጥ ናትና ቤተሳይዳ የምህረት ቤት ናት። አምስቱ አዕማድም የተባሉትም 1) ምስጢረ ሥላሴ 2) ምስጢረ ሥጋዌ 3) ምስጢረ ጥምቀት 4) ምስጢረ ቁርባን እና 5) ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን የሚባሉ ናቸው። እንግዲህ ወደዚች የምህረት ቦታ፣ የፀበል ቦታ በመጀመሪያ ሄዶ የተገኘ፣ ገብቶ የተጠመቀ፣ ካለበት ሕመም ሁሉ ፍጹም ጤነኛ ይሆናል። ይህም ሰው 38ዓመት ሙሉ በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ወደ ጸበሏ የሚወስደው፣ በርትቶ ጸንቶ ጠብቆ በሰው ፊት የሚያስገባው ሰው አጥቶ ለብዙ ዘመናት በተስፋ መቁረጥ ላይ ይገኝ የነበረ ነበር።

 

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

መጋቤ ብሉይ አእምሮ ዘውዴ

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ  አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት፤ በነቢያት  ሲነገር፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡
ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

(ጸሎተ ኪዳን - ዘሠርክ)

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ቤተ ክርስቲያን የምንላት ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍጹምና ከማይነገር ፍቅሩ የተነሣ ሰው እስከ መሆን፣ ሰው ሆኖም በዚህ ዓለም ከኃጢአት በስተቀር እንደ ሰው መኖርን፣ ከዚያም በቀራንዮ ቅዱስ ሥጋውን እስኪቆርስላትና ክቡር ደሙን እስኪያፈስላት ድረስ የደረሰላትና የመሠረታት የምእመናን አንድነት (ጉባኤ) ናት፡፡ "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት" የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል መሠረትነት በኢየሱስ ክርስቶስ ራስነት በምእመናን አካልነት የተመሠረተች ጉባኤ ናት፡፡

   ተጨማሪ ያንብቡ
  


ስብከተ ወንጌል

በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና


በምክረ ከይሲ ተታልለው ትዕዛዘ እግዚአብሔርን የጣሱት አዳምና ሔዋን ዕራቁታቸውን እንደሆኑ ባወቁ ጊዜ የበለስን ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም በማድረግ የአምላካቸው የእግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰምተው በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ ወዴት ነህ? አለው። /ዘፍ. ፫፥፯-፱/።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

ትንሣኤ (በመልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን)

በአርዓያ ሥላሴ የተፈጠረው አዳም

አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ፍጥረታትን ለተከታታይ አምስት ቀናት ከፈጠሩ በኋላ በስድስተኛው ቀን /ዓርብ/ በነግህ እንዲህ አሉ።  ‹‹ንግበር ሰብአ በአርዓያነ ወበአምሳሊነ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር›› /ዘፍ ፩፥፳፮/።  ሥላሴ በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ማለታቸው እንዴት ነው ቢሉ ሥላሴ ለባውያን፣  ነባብያን፣  ሕያዋን ናቸው።  አዳምም ለባዊ፣  ነባቢ፣  ሕያው ነው።  ሥላሴ ፍጹም መልክእ እንዳላቸው አዳምም ፍጹም መልክእ  አለው።  ሥላሴ በልብ በቃል፣  በእስትንፋስ ይመሰላሉ ለሰውም ልብ፣  ቃል፣  እስትንፋስ አለው። ሥላሴ በባሕርያቸው የሚገዙትን አዳም በጸጋ እንዲገዛ ሥልጣን ሰጥተውታል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 3 of 6First   Previous   1  2  [3]  4  5  6  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement