View in English alphabet 
ረቡዕ ታህሳሥ ፴ ፳፻፲፯ ዓ/ም  | Wednesday, January 8, 2025 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ኅብረ ነገር

የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን ዕረፍት 21ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. የተካሔደ የስልክ ኮንፈረንስ መርሐ ግብር

  


ዜና

ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፥ በሰሜን አሜሪካ የምዕራብ ስቴቶችና የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የ2004 ዓ. ም. አዲስ ዓመት በዓልን አስመልክተው ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትና ቃለ ቡራኬ።


ብፁዕ አቡነ አብርሃም፥ የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የ2004 ዓ. ም. አዲስ ዓመት በዓልን አስመልክተው ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትና ቃለ ቡራኬ።

  


ስብከተ ወንጌል

በዲ/ን አብነት አረጋ


“በቸርነትህ ዓመት ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል ኮረብቶች በደስታ ይታጠቃሉ። ማሠማሪያዎችም መንጎችን ለበሱ ሸለቆዎችም በእህል ተሸፈኑ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምሩማል”  /መዝ ፷፬(፷፭)፥፲፩-፲፫/
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገርዎ!
  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ ሞይስስና እኅቱ ሣራ በሰማዕትነት ያረፉበት ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ “መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፤ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል፤ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት አይቻለውም” በማለት እንዳስተማረ የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው መልካም ፍሬን እንዳፈራው ዛፍ ደጎችና እጅግም ባለጸጎች ነበሩ። /ማቴ. ፯፥፲፯-፲፰/
  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

ብዙውን ጊዜ “ጠቢቡ” የሚለው ቃል ይቀጸልለታል። በእርግጥም በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ንጉሥ ሆኖ በተሾመ ጊዜ በፍጹም አትኅቶ (ራስን ዝቅ በማድረግ) “መልካሙንና ክፉውን ይለይ ዘንድ ለባሪያህ አስተዋይ ልቡናን ስጠው” በማለት ከብርና ከወርቅ ይልቅ የበለጠውን ነገር በመለመኑ እግዚአብሔር ተደሰተበት። “እኔ እንደቃልህ አድርጌልሀለሁ እነሆ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ ከአንተም በኋላ እንዳይነሳ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሀለሁ” ተባለ። /፩ ነገ. ፫፥፱-፲፬/ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ከ፲፻፲፱-፱፻፸፱ ዓ.ዓ. የነገሠው ሰሎሞን።

ሰሎሞን እጅግ በጣም በጥበብና ልብን በሚነኩ ምሳሌዎች የተሞሉ አምስት መጻሕፍትን ደርሷል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ “መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን” ይባላል። ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር እንደማለት ነው። በዚህ መጽሐፍ እግዚአብሔር አምላካችን በገለጠለት መጠን በሴት አንቀጽ እየጠራና በፍቅር እየመሰለ ስለሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንና ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ምሥጢር ተናግሮበታል።
  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 23 of 41First   Previous   18  19  20  21  22  [23]  24  25  26  27  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement