ትምህርተ ሃይማኖት
ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፤ ምክንያቱም የአንድ የክርስቶስ አካል ናትና። ይህች የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስርስቲያን መሠረቷም ጉልላቷም ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንንም ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ፦ «እርሱም (ክርስቶስ)ከሁሉ በፊት ነው፤ (ለዘመኑ ጥንት የሌለው ቀዳማዊ ነው)፤. . . እርሱም የአካሉ ማለትም የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤. . . እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት፤» ሲል ገልጦአታል። ኤፌ ፩፥፳፫፣ ቈላ ፩፥፲፰። በተጨማሪም በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ «የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ ሊመሠርት አይችልምና፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።» ብሎአል። ፩ኛ ቆሮ ፫፥፲-፲፩።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኪነ ጥበብ
በዲ/ን አብነት አረጋ
የኑፋቄ ትምህርት እንክርዳድ ቢዘራ
ያሸነፈ መስሎት አሕዛብ ቢያቅራራ
ወጀብ ቢወጅብም ቢነሳ ዐውሎ ነፋስ
ውቅያኖስ ቢያናውጽ ዛፍን ቢገረስስ
ንውጽውጽታ በዝቶ ቢሰማ ነጐድጓድ
ሜዳው ቢጥለቀለቅ ተራራውም ቢናድ
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኅብረ ነገር
በእንተ ስማ ለማርያም፤ በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ዐውደ ርዕይ እና የውይይት መርሐ ግብር
|
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
፩. መግቢያ
ዜማ የሥራና የምስጋና ፍጡራን ሆነው ለተፈጠሩት ሰው እና መላእክት ከእግዚአብሔር የተሰጠ የጸጋ ስጦታ ነው። በዜማ ማመስገን ዋጋው እጥፍ ድርብ ከመሆኑም በላይ በንባብ ከማመስገን በበለጠ ሁኔታ መንፈሳዊ ተመስጦን የሚያመጣ በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች እግዚአብሔርን በዜማ ሲያመሰግኑ ኖረዋል።
ሙሉውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።
|
ኅብረ ነገር
መንፈሳዊ ግብዣ
«ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።» /መዝ. ፻፴፫፥፩/
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|