View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ፕሮጀክቶች

“በዝርወት ባለች ቤተክርስቲያን የሕፃናት መንፈሳዊ ትምህርት ማስተማሪያ ቋንቋ” በሚል ርዕስ ላይ የተካሔደውን ጥናት ውጤት ለማንበብ ይህንን  ይጫኑ።

  


ዜና

“የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” በሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር መነሻነት ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ” በሚል ርዕስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ያረፉበት ፳፩ኛ ዓመት (ሐምሌ ፳፪) በልዩ  መርሐ ግብር ታስቦ ውሏል። በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል የተዘጋጀው ይኸው የመታሰቢያ ዝግጅት ሁለት ሰዓት ተኩል የፈጀ የስልክ መርሐ ግብር ሲሆን በአሜሪካ ማዕከል ውስጥ ባሉ አስራ አንድ ቀጣና ማዕከላት የሚገኙ የማኅበሩ አባላትና ምዕመናን ተሳትፈውበታል::  በዝግጅቱ ላይ የብፁዕ አባታችን አጭር የሕይወት  ታሪክ ከተነበበ በኋላ  እና ብፁዕነታቸው ባቋቋሙት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሰልጠኛ በመግባት ከእግራቸው ሥር ቁጭ ብለው ወንጌልን በሕይወት ከተማሩት፣ የአባታችንን የሕይወት እና የአገልግሎት ፍሬዎች በዓይናቸው ከተመለከቱት እና መጽሐፎቻቸውን በጥልቀት ካነበቡት አባቶች እና ወንድሞች መካከል መልአከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው ወርቁ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን እና ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ምስክርነታቸውን ጥልቅ በሆነ የፍቅር ስሜት ገልጸዋል።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ማኅበረ ቅዱሳን

የሕይወት ታሪክ እና አገልግሎታቸው

መግቢያ

ዛሬ የሚያውቋቸው ሲቃ ይተናነቃቸዋል። ዓይናቸው በእንባ ይሞላል። ስለብፁዕነታቸው ሲያወጉ ውለው ቢያድሩ አይሰለቹም። እንኳን ዘዋይ ደርሰው የመጡት ፊታቸውን እንኳን አይተው የማያውቁት የብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስን ዜና ሕይወት መተረክ ያስደስታቸዋል። ለምን ይሆን? ብዙዎች በአካል ሳያውቋቸው ጣፋጭ ትምህርታቸውን ከአንደበታቸው ሳያዳምጡ በማለፋቸው ይቆጫሉ። ሌሎች ደግሞ ትምህርታቸውን፣ ምክራቸውን፣ ሓሳባቸውን ሁሉ በምስል እና በድምጽ ሳያስቀሩ በማለፋቸው ይጸጸታሉ። ሐዋርያዊ ተጋድሎዋቸው እና መንፈሳዊ አርበኝነታቸውን በቅርብ ላስተዋለ እና ዜና ሕይወታቸውን ላዳመጠ ብፁህነታቸው ዘወትር የሚነበቡ ታላቅ መጽሐፍ ነበሩ። የቅንጦት እና የቅምጥል ሕይወት ሳይናፍቃቸው በፍጹም ገዳማዊ ጠባይ የላመ የጣመ ሳይመገቡ፣ በትኅርምት እየኖሩ ወላጅ አልባ እና ችግረኛ ህጻናትን ሰብስበው እያሳደጉ ቢንቢ እየወረሳቸው ዋዕዩ  በሚፋጅበት የወባ በሽታ ባየለበት ሌላው ቀርቶ ጣፋጭ እና ንጹህ ውሃ እንኳን በማይገኝበት ስፍራ ራሳቸውን ጥለው በበሽታ ሲሰቃዩ  አንድ ቀን እንኳን ሳይሰለቹ እና ሳይማረሩ በተጋድሎ የኖሩ እጅግ ትሁት የነበሩ አባት ነበሩ። በመንፈስ የወለዷቸው፣ በሃይማኖት ያሳደጓቸው ልጆቻቸው ከልብ በመነጨ ፍጹም ፍቅር “ጎርጎሪ” እያሉ ሲጠሩዋቸው የሰማ የብፁዕነታቸውን ታሪክ ለማወቅ ይጓጓል።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ለተነሱ ወቅታዊ ጉዳዮች ከማኅበሩ የተሰጠውን ማብራሪያ ይህንን  በመጫን ያንብቡ::

  


ነገረ ቅዱሳን

ባለፈው የሁለተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዜና ሕይወትና ሰማዕትነት እንዴት እንደ ተቀበሉ ተመልክተናል። አሁን ደግሞ ከቅዱስነታቸው 43 ዓመታት በፊት በፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጁትን የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ ዜና ሕይወትና የሰማዕትነት ታሪክ እናቀርባለን።

በ1875 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸው ገና በወግ ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ባሕታዊ ተድላ ለተባሉ መምህር አደራ ሰጧቸው። በዚያው ገዳም የንባብ ቤቱንና የዜማውን የትምህርት ደረጃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜ አቀላጥፈው በመጨረስ ገና በልጅነት የዕድሜ ደረጃቸው ሦስተኛውን የቅኔ ትምህርት ጀምረው በአጭር ጊዜ ሙሉ ቤት ተቀኙ። ይህንኑ የቅኔ ትምህርት ለማስፋፋት በምዕራብ ጎጃም አገረ ስብከት ወደሚገኘው የቅኔ ትምህርት ማዕከል ዋሸራ ተሻግረው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈጽመው አስመሰከሩ።
  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 24 of 41First   Previous   19  20  21  22  23  [24]  25  26  27  28  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement