ነገረ ቅዱሳን
ይህች ቅድስት ከኒቆምድያ ሀገር በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን ሐዋርያዊት የሆነች ናት። ቅዱስ ጳውሎስም ከአንጾኪያ ከተማ በወጣ ጊዜ፤ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ሄደ። በዚያም ስሙ ስፋሮስ የሚባል ምዕመን ሰው ነበር። ቅዱስ ጳውሎስን ወስዶ በቤቱ አኖረው፤ ብዙ አሕዛብም የሐዋርያው የጳውሎስን ትምህርት ይሰሙ ዘንድ በእርሱ ዘንድ ይሰበሰቡ ነበር።
ይህች ቅድስት ቴክላም በቤቷ መስኮት ተመለከተች፤ የሐዋርያውንም ትምህርት ሰማች። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ፈታኝ ቀርቦ፤ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ፤ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል።” ብሎ እንደመለሰለት እንዲሁም ትምህርቱን እያዳመጠች ሳትበላና ሳትጠጣ ሦስት ቀኖች ቆየች። ትምህርቱም በልቧ አደረ፤ አባትና እናቷ ቤተሰቦቿም ሁሉ አዘኑ። ከምክርዋም እንድትመለስ ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዳትከተል ለመኗት፤ ነገር ግን አልሰማቻቸውም። /ማቴ. ፬፥፫-፬/።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኅብረ ነገር
በአሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ታላቁ ሐዋርያዊ አባት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ያረፉበትን 21ኛ ዓመት (ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም) መታሰቢያ በማድረግ የብጹዕነታቸውን ታላቅ ሐዋርያዊ አገልግሎትና ሥራቸውን ለመዘከር፣ የእርሳቸውም በረከት እንዲያድርብን በማሰብ “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ” የሚል የስልክ መርሐግብር አዘጋጅቷል:: በመርሐግብሩ ላይ ብጽዕነታቸውን በቅርብ ከሚያውቁ አባቶችና ደቀመዝሙሮቻቸው ዝግጅቶች ይቀርባሉ።
መርሐግብሩ የሚካሄድበት ቀን:- እሑድ ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ/ም / July 31, 2011
ሰዓት፦ ከቀኑ 6:00 PM – 8:00 PM EST / 3:00 PM – 5:00 PM PST
ውይይቱ የሚካሄድበት ኮንፈረንስ ስልክ:- ለማዳመጥ ብቻ፦ 712 432 1001 ፒን፦ 428585128
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ነገረ ቅዱሳን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን ሁለንተናዊ ማንነት ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይት ናት ሲባል ሁልጊዜ እንደሚባለው በሥነ ጽሑፍ ወይም በሥነ ሕንፃው፣ በሥነ ሥዕሉ ወይም በሥነ ትምህርቱ ብቻ አይደለም። ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ማንነት ላይ የነበራትና ያላት አስተዋፅዖ ፍጹም ስለሆነ ለአገሪቱ የመጣን ደግ ነገር የመካፈሏን ያህል ጉዳቷንም ተቀብላለች። ኀዘኗን አዝናለች፣ ሕማሟን ታማለች። የአገሪቷም ሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ያለፈ ታሪክ የሚያስረዳን ይኽንኑ ነው።
ጥንት የሚባለው ታሪካችን እንዳለ ሆኖ ባለፉት መቶ ዓመታት የተመዘገበውን ታሪክ ብንመለከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን በተከሰተው ውጣ ውረድ ቀደምት ተጠቂ እንደሆነች እንረዳለን። ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ህልውና የቤተ ክርስቲያን ሚና ወሳኝ እንደሆነ ያረጋግጣል።
በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ወልዳ ለወግ ለማዕረግ ካበቃቻቸው በኋላ የሰጠቻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደፋ ቀና ሲሉ በገፋዕያን የተገደሉትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ዜና ሕይወትና የሰማዕትነት ዕረፍት እናዘክራለን።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ማኅበረ ቅዱሳን
መላከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው ወርቁ ከማኅበረ ቅዱሳን መስራች አባላት አንዱ ሲሆኑ የመጀመሪያው የማኅበሩ ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅ፣ እና የመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የራቸስተር ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና የማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል ሰብሳቢ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። የዚህ ዕትም የሐመረ ኖኅ እንግዳ አድርገናቸዋል፤ ተከታተሉን።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ስብከተ ወንጌል
በቀሲስ ፋሲል አስረስ
“ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ። ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥ ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ” ማር. ፫፥፲፫-፲፮።
የተመረጡት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው። ሐዋርያ ማለት ሖረ፣ ሄደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን የተላከ፣ ሂያጅ፣ ልዑክ ማለት ነው። ሐዋርያት በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተጠርተው እነርሱም ጥሪውን ተቀብለው እንደሔዱ እንረዳለን። ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው።
በዚህ አጭር ጽሑፍ የሚከተሉትን ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች እንመለከታለን፦
• መጠራት
• ከእርሱ ጋር መኖር /ከእግዚአብሔር ጋር መኖር/
• ለመስበክ መላክ /ለአገልግሎት መላክ/
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|