View in English alphabet 
 | Monday, December 30, 2024 ..:: ትምህርተ ሃይማኖት ::.. Register  Login
ክርስቲያናዊ ሕይወት, ትምህርተ ሃይማኖት

ምሥጢረ ቁርባን ማለት ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በመሞቱ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደበት፣ የዘላለም ሕይወትን ያሰገኘበት፣ የመዳናችን መሠረት፣ የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ጸጋ የሚያመለክት ታላቅ የክርስትና ሃይማኖት ምሥጢር ነው። ክርስቶስ እንደ መሥዋዕትም እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትም በመሆን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ፈጽሟል (ዕብ ፯፣፳፡፳፰)። እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትነቱ በመስቀል ላይ የተቆረሰው ሥጋውን የፈሰሰው ደሙን የኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረቡ ሰውን ከራሱና ከእግዚአብሔር ጋር አስታራቀ፣ የጥልንም ግድግዳ አፈረሰ፣ የተራራቀውን አቀራረበ።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

በትራክት መልክ የተዘጋጀውን የአማርኛ የጥምቀት መልእክት እዚህ ያግኙ
Find the English Epiphany message in a tract form here


የጥምቀት አስፈላጊነት

በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና



በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከኒቂያ ጉባኤ በኋላ ከተነሱት አባቶች አንዱ “በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም” ራእይ ፳፥፮ የሚለውን የወንጌላዊው ዮሐንስን አባባል በተረጎመበት የእግዚአብሔር ከተማ በሚለው መጽሐፉ ላይ ፊተኛው ትንሣኤ የተባለው ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና የምናገኝበት ጥምቀት እንደሆነ ገልጿል (De Civitate Dei,xx,6)።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::

  ከጌታችንና ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት መስቀል የመቅጫ መሣሪያ ነበር። ሰውን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረውም በፋርስ ነው። ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ናት። የፋርስ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የተባለ “የመሬት አምላክ” ያመልኩ ነበር። ከዚህም የተነሣ “ወንጀለኛው ቅጣቱን በመሬት ላይ የተቀበለ እንደሆነ አምላካችን ይረክሳል፤” ብለው ስለሚያምኑ ወንጀለኛውን ከመሬት ከፍ አድርገው በመስቀል ላይ ይቀጡት ነበር። ይህም ቅጣት ቀስ በቀስ በሮማ ግዛት ሁሉ የተለመደ ሕግ ሆነ። ከዚህም ሌላ በኦሪቱ ሥርዓት ቅጣታቸውን በመስቀል ላይ የሚቀበሉ ሰዎች ርጉማንና ውጉዛን ነበሩ። ይህንንም እግዚአብሔር ለሙሴ “ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥ በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር፤” ሲል ነግሮታል። ዘዳ.21፥22-23። እዚህ ላይ “በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሚሞት የተረገመ ከሆነ፥ ለምን ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ?” እንል ይሆናል። ይህንንም እንደሚከተለው እናያለን።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

ደብረ ዘይት
/ማቴ. ፳፬፥፩-ፍጻሜ/

በትራክት መልክ የተዘጋጀውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ከፈለኝ ወልደጊዮርጊስ

 

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል። ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው። በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩ ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ኀጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን”
/ጸሎተ ሃይማኖት/

ጥምቀተ ክርስቶስ

ለጌታችን ሠላሳ ዓመት ሊሆነው ስድስት ወር ሲቀረው ፣ የሊቀ ካህናቱ የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ ከምድረ በዳ ወጥቶ ማስተማር ጀመረ:: ይህንንም ትምህርት የጀመረው ከፈጣሪው ባገኘው መልእክት ነው:: ሉቃ ፫፥፩ ዮሐንስም ከቆሮንቶስ ምድረ በዳ ወጥቶ በዮርዳኖስ ዙርያ “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ በማስተማር የንስሐን ጥምቀት ማጥመቅ ጀመረ :: ሉቃ ፫፥፫ ሕዝቡም ትምህርቱን በመቀበል ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ በንስሐ ጥምቀት ይጠመቁ ነበር:: ማቴ ፫፥፫ የትምህርቱን እውነተኛነት ባወቁ ጊዜ ዮሐንስን ክርስቶስ ነው ብለው ጠረጠሩ:: ሉቃ ፫፥፲፭ ዮሐንስም እንዲህ ሲል እውነቱን ነገራቸው " እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ። የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ። የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና። እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።  ዮሐንስ መልሶ፦ እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል፤  እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው አላቸው። ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ። በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።" ዮሐ ፩፥፳

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 2 of 7First   Previous   1  [2]  3  4  5  6  7  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement