አንድ ሰው ለጉዞ ሲነሣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ በዐቢይ ጾምም እንዲሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ዐቢይ ጾም መንፈሳዊ ጉዞ ነው፤ መድረሻውም ትንሣኤ ነው፡፡ ለእውነተኛው መገለጥ ለፋሲካ መሟላት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡ ስለዚህ በጣም አስፈላጊ የሆነና ስለ ክርስትና እምነታችንና ሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ስለሚገልጥልን ይህን በዐቢይ ጾም እና በትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በመሞከር መጀመር አለብን፡፡
መልእክቱ ለዕብራውያን የተጻፈ መልእክት ነው። ዕብራውያን የሚለው ስያሜ ምን አልባትም ከአብርሃም ቅድመ አያት ከነበረው “ከዔቦር” ስም የተመሠረተ ሊሆን እንደሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። መልእክቱ የተጻፈበት ዘመን ሮማውያን የኢየሩሳሌምን ቤተመቅደስ ካፈረሱበት ከ70 ዓ.ም. በፊት በ60ዓ.ም. እንደሆነ ይነገራል። በዕብራውያን ያሉትን መልእክታት ስንመለከታቸው በብሉይ ኪዳን ይከናወኑ የነበሩትንና ይደረጉ የነበሩትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እንዴት እና ምን ይመስሉ እንደ ነበር፣ እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ያሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና አስተምህሮዎች ላይ ያተኮረ ነው::
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዱሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ2003 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ
የመግለጫው ሙሉ ቃል ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ
ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ- የሰሜን ምዕራብ አሜሪካ፣ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የ2003 ዓ.ም የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ
ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።