View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: ነገረ ቅዱሳን ::.. Register  Login
ነገረ ቅዱሳን

 

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን ሁለንተናዊ ማንነት ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይት ናት ሲባል ሁልጊዜ እንደሚባለው በሥነ ጽሑፍ ወይም በሥነ ሕንፃው፣ በሥነ ሥዕሉ ወይም በሥነ ትምህርቱ ብቻ አይደለም። ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ማንነት ላይ የነበራትና ያላት አስተዋፅዖ ፍጹም ስለሆነ ለአገሪቱ የመጣን ደግ ነገር የመካፈሏን ያህል ጉዳቷንም ተቀብላለች። ኀዘኗን አዝናለች፣ ሕማሟን ታማለች። የአገሪቷም ሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ያለፈ ታሪክ የሚያስረዳን ይኽንኑ ነው።

ጥንት የሚባለው ታሪካችን እንዳለ ሆኖ ባለፉት መቶ ዓመታት የተመዘገበውን ታሪክ ብንመለከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን በተከሰተው ውጣ ውረድ ቀደምት ተጠቂ እንደሆነች እንረዳለን። ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ህልውና የቤተ ክርስቲያን ሚና ወሳኝ እንደሆነ ያረጋግጣል።

በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ወልዳ ለወግ ለማዕረግ ካበቃቻቸው በኋላ የሰጠቻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደፋ ቀና ሲሉ በገፋዕያን የተገደሉትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ዜና ሕይወትና የሰማዕትነት ዕረፍት እናዘክራለን።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር በመንፈሳዊ አገልግሎት ባዘነበሉ መጠን ቸርነት የባሕርዩ የሆነ እግዚአብሔር ደግሞ የተለያየ መንፈሳዊ ብቃትን ይሰጣቸዋል፤ ሰማያዊ ምሥጢርን ይገልጥላቸዋል። ቅዱሳን በሥጋቸው በምድር ለጸሎት ቆመው ነፍሳቸው በተመስጦ ገነት መንግሥተ ሰማያት ተነጥቃ ሄዳ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ታመሰግናለች። እንዲሁም በአካል እንደ ነቢያቱ ሄኖክና ኤልያስ በመወሰድ እስከ ጌታችን ዳግም ምጽአት መዳረሻ ቀን በመሰወር እንደሚኖሩ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዱናል።

«መሰወር» የሚለው ቃል የግእዝ ግሱ «ኀብአ»፦ «ሰወረ፥ መሰወር»፤ «ተኀብአ»፦ «ተደበቀ፥ ተሰወረ፥ ራቀ፥ ረቀቀ» ማለት ሲሆን በጥቅሉ ለዓይን እንዳይታይ እንዳይገኝ ሆነ፤ ለምሥጢርም ከሆነ ለአእምሮ ረቀቀ ማለት ነው ።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚጠቀሱት ውስጥ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

 

ከመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው
 «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤»  መኃ 4:7

የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ ፡-የስብከተ ሐዋርያት መነሻ.የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ነገረ ማርያም ነው፡፡ ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን መናገር አይቻልም፡፡ በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ የተነሡ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው የነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር ፡፡ ያም ችግራቸው ክርስቶስን በትክክል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል፡፡ በነገረ ማርያም ላይ የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኖሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር ፡፡ ንስጥሮስ፡- «አምላክ ወልደ አምላክ» ብሎ በክርስቶስ ለማመን የተሳነው « ወላዲተ አምላክ . ወላዲተ ቃል. እመ እግዚአብሔር » ብሎ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ለማመን በመቸገሩ ነበር፡፡  PDF

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

 ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል፡፡ እንዲያውም ‹‹አላዋቂ ሳሚ...›› እንዲሉ ስለ እመቤታችን ማስተማå ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም፡፡  ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኰት ምሁርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 4 of 5First   Previous   1  2  3  [4]  5  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement