View in English alphabet 
 | Sunday, December 22, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ነገረ ቅዱሳን

ከብርሃኑ ጎበና

ቅዱስ ማለት የተለየ፣ የተከበረ፣ የተመሰገነ፣ የተመረጠ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ስንልም የተመሰገኑ፣ ከርኵሳን መላእክት የተለዩ፣ ክቡራን መላእክት ማለታችን ነው፡፡ መላእክት ሁለት ወገን ናቸው፡፡ ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የሆነው የዲያብሎስ ሠራዊት የሆኑት እኩያን መላእክት፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ቸርነትን ወደ ሰው ልጆች፣ የሰዎችንም ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ ናቸው፡፡

ስለ ተራዳኢነታቸው - በቅዱሳት መጻሕፍት

ቅዱሳን መላእክት በመንገዳችን ሁሉ እንደሚጠብቁን ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል «በመንገድ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንነተ ያዝዛቸዋልና፣ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል» (መዝ. 90/91/-11)፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


ማኅበረ ቅዱሳን

በአሁኑ ሰዓት በሰሜን አሜሪካ የምዕራብ ስቴቶችና ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት በሥራ አስኪያጅነት እንዲሁም ዴንቨር፣ ኮሎራዶ በሚገኘው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአስተዳዳሪነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከግብፅ የቲዮሎጂ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነው አገልግሎታቸውን የጀመሩ ሲሆን  በቀጣዮቹ ዓመታት ወደ አሜሪካ እስከመጡበት ጊዜ ድረስ የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ፣ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምክትል ዲን እንዲሁም የቅዱስ ጳውሎስ ሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን በመሆን ሲሠሩ ቆይተዋል። በአንድ ወቅት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተደርጐ በነበረውና ከፍተኛ ውጤት በታየበት የአገልግሎት ጉዞ ልኡካን ከነበሩት አራት አባቶችም አንዱ ነበሩ። ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ አለማየሁ። እኛም ስለአገልግሎታቸው እና የሕይወት ተሞክሯቸው እንዲያካፍሉን የእዚህ ዕትም የሐመረ ኖኅ እንግዳ አድርገናቸዋል። ይህንን ለማሳካት ላደረጉልን ትብብር ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን ወደ ቃለ ምልልሱ እናሸጋግራችኋለን። መልካም ንባብ።

ሙሉ ንባቡን እዚህ ያገኙታል
ሐመረ ኖኅ ኤሌክትሮኒክስ መጽሔት፣ ነሐሴ ፳፻፫ ዓ.ም.
  


ኪነ ጥበብ

በዲ/ን አብነት አረጋ


በገሊላ ቃና በዶኪማስ ቤት
ድንግል አዛኚቱ የአምላክ እናት
እድምተኛው በዝቶ ወይኑ ቢያልቅባቸው
ጥብብ ጭንቅ ሲሉ ማጣፊያው አጥሯቸው
ወይ ጓዳ ሳትገባ ሳትጠይቃቸው
  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ከጥቅምት ፲፯ እስከ ፲፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በኮሎምበስ፣ ኦሃዮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው የመምህራንና ዘማርያን የምክክር ጉባኤ በታላቅ ድምቀት ተካሒዷል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 21 of 41First   Previous   16  17  18  19  20  [21]  22  23  24  25  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement