ኅብረ ነገር
እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን፣ በባሕር የሚዋኙትንና በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈባት ዕለት ዕለተ ቅዳሜ ናት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኅብረ ነገር
የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሰንበትና ሳምንቱ ኒቆዲሞስ ይባላል። ኒቆዲሞስ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሰንበት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ «ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ መልአኮሙ ለአይሁድ ዞሖረ ኃቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ወይቤሎ ለኢየሱስ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡- ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል የአይሁድ አለቃ የሆነ ከፈሪሳውያን ወገን አንድ ሰው ነበረ፡፡ እሱ አስቀድሞ ሌሊት ሄዶ ኢየሱስን በመቃብር አንቀላፋህ በትንሣኤህ አንሣኝ» ያለው ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኅብረ ነገር
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፡፡ ገብር ሔር ወገብር ምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሰይመከ፡፡ በጥቂቱ የታመንህ ቸር አገልጋይ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ…›› ስለሚል ነው፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
|
ኅብረ ነገር
በቅርቡ ተደርጎ የነበረው የ1999 ዓ.ምሕረቱ የሕዝብ ቆጠራ ከቤተ ክርስቲያናችን አንጻር ስላለው ምንነት የተዘጋጀውን የፍኖተ ሰላም ሬዲዮ ዝግጅት ያዳምጡ።
የሕዝብ ቆጠራው የልዩ ዝግጅታችን አካል የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ቆጠራውና ውጤቱ በጉጉት ሲጠበቅ ስለነበርና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኩልም የሚኖረው ትርጉም ሰፊ ስለሚሆን ነው።
በጠቅላላው በቆጠራውና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ጋር ቆይታ አድርገናል እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት በአድራሻችን ይላኩልን።
|
ኅብረ ነገር
ምክሮች - 1
• የሕይወት መገኛ የሆነውን አምላክህን እወቅ፡፡ በእርሱም ታመን፡፡ እርሱንም ተስፋ አምባና መጠጊያ በማድረግ ኑር፡፡
• ሕይወት ውጣ ውረድ የሚበዛባት ደስታና ሐዘን የሚፈራረቅባት መድረክ በመሆኗ ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው በትእግሥትና በማስተዋል ለማሳለፍ ተጣጣር፡፡
• በሕይወት ዘመንህ በምታፈራው ገንዘብ የተራበን በማብላት የተጠማን በማጠጣት የታረዘን በማልበስና ችግረኞችን በመርዳት ጽድቅንና መልካም ስምን አትርፍበት፡፡
• ሕይወት በብቸኝነት እጅግ መራራ ናትና በጊዜ ከአምላክህ ጋር ተነጋግረህ የኑሮ ጓደኛህን በመምረጥ በመፈቃቀር በመተሳሰብና በመተጋገዝ ለመኖር ተዘጋጅ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|