View in English alphabet 
 | Friday, June 14, 2024 ..:: ስብከተ ወንጌል ::.. Register  Login
ስብከተ ወንጌል

በቀሲስ ፋሲል አስረስ


“ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ። ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥ ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ” ማር. ፫፥፲፫-፲፮።

የተመረጡት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው። ሐዋርያ ማለት ሖረ፣ ሄደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን የተላከ፣ ሂያጅ፣ ልዑክ ማለት ነው። ሐዋርያት በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተጠርተው እነርሱም ጥሪውን ተቀብለው እንደሔዱ እንረዳለን። ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው።


በዚህ አጭር ጽሑፍ የሚከተሉትን ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች እንመለከታለን፦
• መጠራት
• ከእርሱ ጋር መኖር /ከእግዚአብሔር ጋር መኖር/
• ለመስበክ መላክ /ለአገልግሎት መላክ/

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል


ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል
    ዕብ. ፲፩፥፬
(በመምህር ቀሲስ ስንታየሁ ደምስ ከሚኒሶታ)


መልእክቱ ለዕብራውያን የተጻፈ መልእክት ነው። ዕብራውያን የሚለው ስያሜ ምን አልባትም ከአብርሃም ቅድመ አያት ከነበረው “ከዔቦር” ስም የተመሠረተ ሊሆን እንደሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። መልእክቱ የተጻፈበት ዘመን ሮማውያን የኢየሩሳሌምን ቤተመቅደስ ካፈረሱበት ከ70 ዓ.ም. በፊት በ60ዓ.ም. እንደሆነ ይነገራል።
በዕብራውያን ያሉትን መልእክታት ስንመለከታቸው በብሉይ ኪዳን ይከናወኑ የነበሩትንና ይደረጉ የነበሩትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እንዴት እና ምን ይመስሉ እንደ ነበር፣ እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ያሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና አስተምህሮዎች ላይ ያተኮረ ነው::   ተጨማሪ ያንብቡስብከተ ወንጌል

(ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ማታ እየወጣ የሚያድርባት፣ሐሙስ ሌሊት በይሁዳ በኩል ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠባት፣ሐዋርያት ስለ ነገረ ምጽአት ጠይቀው የተረዱባት፣ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ጌታችን ያረገባት ተራራ -ደብረ ዘይት። ዐርገ የሚለው የግዕዝ ግስ ዐረገ፣ወጣ በሚሉት የአማርኛ ቃላት የሚፈታ ሲሆን ዕርገት የሚለው ስምም ማረግን፣ መውጣትን፣አወጣጥን ያመለክታል።(አ.ኪ.ክ መ.ቃ)

አስቀድሞ ክቡር ዳዊት እንደተናገረው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ እያዩት ወደ ሰማይ ዐርጓል። ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ወእግዚእነ በቃለ ቀርን - እንዲል መዝ. 46፥5። ጌታችን በእውነት እንዳረገ ይኽም ሊታመን የማይችል እንዳልሆነ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስረዳል። ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሄደ፡ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፤ሥጋው አልተለወጠምና። ሃይ.አበው ዘዮሐ.አፈ.ክፍል 13 ቁጥር 15

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

(በቀሲስ ስንታየሁ አባተ)
በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው:: እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው:: ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃስ ወንጌል ምዕ. 18¸12 ላይ ያለው ቃል ያስረዳል:: ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትንና ከዚያ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበR:: በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል::"የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአስረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ" ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበረ:: ዘካ. 8 18ና19

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

 

ሕዝ 347
                      መምህር ዕርገተ ቃል ይልማ

ከዐበይት ነቢያት አንዱ የሆነው ሕዝቅኤል ከጌታ ልደት 597 ዓመት በፊት የተነሳ ነቢይ ነው፡፡ይህ ታላቅ ነቢይ የእሥራኤል ልጆች ወደ ባቢሎን ተማርከው በስደት በሄዱ ጊዜ

ከምርኮኞች አንዱ በመሆን እስራኤላውያን የደረሰባቸውን መከራና ስቃይ በዐይኑ ለማየት ጩኸታቸውንም በጆሮው ለመስማት ችሏል፡፡ ኢየሩሳሌም ለከፋ ውድቀት ከመዳረጓ በፊት ሕዝቡ ራሳቸውን በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እነዲያቀርቡ መክሯል፡፡ይሁን እንጂ ከበደላቸውና ከኃጢአታቸው ተመልሰው በጽድቅ መንገድ ሊጓዙ ስላልቻሉ የተለያየ መከራ ደረሶባቸዋል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 5 of 6First   Previous   1  2  3  4  [5]  6  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement