View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ማኅበረ ቅዱሳን

  


ማኅበረ ቅዱሳን

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ”

ልደተ ክርስቶስን ስናከብር ከላይ የተጠቀሰውን የመላእክት መዝሙር እናስታውሳለን:: ቅዱሳን መላእክት ይህን ሰላምና እርቅን የሚያበስር መዝሙር ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀኙት ለ5500 ዓመታት ጸንቶ  የቆየው  የጥል እና  የመለያየት ዘመን ተፈጽሞ የእርቅና የአንድነት ዘመን መጀመሩን ለማወጅ ነው:: በአዳም በደል ምክንያት ለዘመናት ተለያይተው የነበሩት የሰው ልጆች እና ቅዱሳን መላእክት በጌታ  ልደት ምክንያት ይህን መዝሙር አብረው ለመዘመር ቻሉ:: ሁላችንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆችም በያለንበት ሆነን በዓለ ልደቱን ስናከብር ይህንን መዝሙር በድምቀት እንዘምራለን::

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

በመላከ ሕይወት ቀሲስ ዕርገተቃል ይልማ

ትራክቱን ለማግኘት ይህን ይጫኑ

ቤተልሔም ማለት የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ታሪካዊ ሥፍራ ናት። ዳዊትም ተወልዶ ያደገው፣ ለንጉሥነት የተቀባውና ቤተ መንግሥቱም የነበረው በቤተልሔም ነበር። ስለዚህ በእስራኤላዊያን ታሪክ ውስጥ ቤተልሔም የተወለደ «ቤተልሔማዊ ነኝ» ብሎ ራስን ማስተዋወቅ ክብር ነበረው። ቤተልሔም የእስራኤል መንግሥት ለሁለት ሲከፈል ቀድሞ የነበራት ታላቅነትና ዝና እንዳልነበረ ሆኗል። ከነቢያት ወገን የሆነው ሚክያስ ለማስተማር ሲያልፍ ይቺ ስመ ጥር የሆነችው ከተማ ተፈትታ፣ ምድረ በዳ ሆና፣ ቋያ በቅሎባት ክብሯ ሁሉ ከላይዋ ላይ ተገፎ ተመለከታት። ከተማይቱ እንደዚህ ሆና እንደማትቀር በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ «አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ የይሁዳ ምድር፣ ከይሁዳ ገዥዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና» ሚክ ፭፥፪ ሲል ተነበየላት።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ንቁ

ሐዋርያዊት የሆነች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን እውነተኛውን የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥት ለ2000 ዓመታት በላይ ልጆቿ ስታውጅ እና ስታበስር ኖራለች:: በተለይም የራሷን ፓትርያርክ ሰይማ ከእራሷ ልጆች ኤጲስ ቆጶሳትን እየሾመች አገልግሎቷን መምራት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ በስብከተ ወንጌል እና አስተዳደር በኩል ተሰፋ ሰጪ ውጥኖች ታይተዋል:: ከውጪና ከውስጥ በሚነሱ ፈተናዎች ምክንያት የሚጠበቅባትን አመርቂ እርምጃ መራመድ ግን አልቻለችም::  በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ምእመናንን በምግባር በሀይማኖት አጽንቶ ከበረት ውጭ ያሉትን የአፍሪካና የሌሎች አህጉራት በጎችን ወደ በረቱ ማምጣትና የተከታዩንም ቁጥር ከፍ ማድረግ ይጠበቅባታል:: ሆኖም ግን በተለይ ከ20 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ ቀስ በቀስ እያደገ የመጣው እና እስከ መወጋገዝ ደረጃ ላይ የደረሰው የብፁዓን አባቶች ልዩነት የወቅቱ አውራ የቤተ ክርስቲያን ችግር ሆኖ በጉልህ ይታያል::

  ተጨማሪ ያንብቡ


ፕሮጀክቶች

የ2003 ዓ.ም. ሪፖርት

በ2003 ዓ.ም. ከተሠሩት ሥራዎች በፎቶግራፍ


ለ2004 ዓ.ም. የታቀዱ ሥራዎችን ያካተተ ሊፍሌት

  


Page 19 of 41First   Previous   14  15  16  17  18  [19]  20  21  22  23  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement