የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም የተወከሉ የእምነት አባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ